የኮሮናቫይረስን ለማከም የሦስት መድኃኒቶች ድብልቅ ተስፋ ሰጪ ውጤት አሳየ

ሆንግ ኮንግ ውስጥ ያሉ ተመራማሪዎች የኮቪድ-19 ህሙማንን ለማከም በሦስት ጸረ ቫይረስ መድኃኒቶች ድብልቅ ላይ ያደረጉት ሙከራ አውንታዊ ውጤት እንዳስገኘላቸው አመለከቱ።'ላንሴት'በተሰኘው የህክምና መጽሔት ላይ አርብ ዕለት የወጣ አዲስ ጥናት ላይ እንደተጠቆመው፤ ቀለል ያለ የኮሮናቫይረስ ህመም ያጋጠማቸው ሰዎች ህክምናው ከተሰጣቸው በኋላ በአጭር ጊዜ ውስጥ ከበሽታው እንዳገገሙ ተገልጿል።

በጥናቱ 127 አዋቂዎች ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥም ለ86ቱ ኢንተርፌርኖ ቤታ-1ቢ፣ ኦፒናቪር-ሪቶናቪር እና ሪባቪሪን የተባሉት የሦስት መድኃኒቶች ድብልቅ ተሰጥቷቸው ነበር።

በዚህም የጥናት ውጤቱን ዘገባ ያቀረቡት ተመራማሪዎች እንዳሉት በሙከራው የተገኘው ውጤትን "ጅማሬ ነገር ግን ጠቃሚ" ሲሉ ገልጸው፤ በኮሮናቫይረስ በጠና በታመሙ ሰዎች ላይ የሚደረግን ሙከራ ጨምሮ ሌላ ምርምር እንደሚያስፈልግ አመለክተዋል።

"ያደረግነው ሙከራ ቀለል ባለ ሁኔታ በኮሮናቫይረስ ለታመመ ሰው ላይ ቀድሞ የሚሰጠው የሦስቱ ጸረ ቫይረስ መድኃኒቶች ድብልቅ በህመምተኛው ሰውነት ውስጥ ያለውን ቫይረስ በፍጥነት ለመቆጣጠር ሳይስችል አይቀርም" ሲሉ ምርምሩን የመሩት ባለሙያ ዎክ-ዩንግ ዩን ተናግረዋል።

Share it now!