በአለማችን በተከሰተው የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት በአፍሪካ በተለይም ከሰሃራ በረሃ በታች ባሉ አገራት ኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው የሚገኝ ሰዎች ጤናቸው መታወክ ሊገጥመው ይችላል

በአለማችን በተከሰተው የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት በአፍሪካ በተለይም ከሰሃራ በረሃ በታች ባሉ አገራት ኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው የሚገኝ ሰዎች ከፊታችን በሚመጡት ሁለት ተከታታይ ዓመታት ላይ ጤናቸው መታወክ ሊገጥመው እንደሚችል የአለም ጤና ድርጅት አሳስቧል፡፡
የኮረና ቫይረስ ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸውን ሰዎች ጤና በማወክ ህይወታቸው እንዲያልፍ የሚያደርግ ወረርሽኝ ነው፡፡ በመሆኑም ኤችአይቪ/ኤድስ በደማቸው የሚገኝ ወገኖች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲሁም በኮረና ወረርሽኝ ስጋት ሳይደናገጡ በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ የጤና ተቋማት በማምራት የፀረ- ኤችአይቪ መድሃኒታቸውን በመውሰድ በህክምና ባለሙያዎች በተሰጣቸው መመሪያ መሰረት መድሃኒታቸውን ወስደው ራሳቸውን ከኮረና ቫይረስና ከሌሎች ተጓዳኝ በሽታዎች መጠበቅ አለባቸው፡፡
በአገራችን የኤችአይቪ/ኤድስ ስርጭት ምጣኔ 0.91 ሲሆን በዚህ ስሌት መሰረት 600,000 በላይ ሰዎች ኤችአይቪ በደማቸው እንደሚገኝ እ.አ.አ በ2019 የተደረገው የኤችአይቪ የስርጭት ግምት መረጃ ያሳያል፡፡ በዚህም ኤችአይቪ/ኤድስ በደማቸው ይገኛል ተብለው ከተገመቱት መካካል የጸረ-ኤችአይቪ መድሃኒት የሚጠቀሙት 480,000 በላይ ሚሆኑ ወገኖች እንደሆኑ በ2012 በጀት ዓመት የፌዴራል ኤችአይቪ/ኤድስ መከ/መቆ/ጽ/ቤት ያወጣው መረጃ ያሳያል፡፡

Share it now!
በአለማችን በተከሰተው የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት በአፍሪካ በተለይም ከሰሃራ በረሃ በታች ባሉ አገራት ኤችአይቪ ቫይረስ በደማቸው የሚገኝ ሰዎች ከፊታችን በሚመጡት ሁለት ተከታታይ ዓመታት ላይ ጤናቸው መታወክ ሊገጥመው እንደሚችል የአለም ጤና ድርጅት አሳስቧል፡፡
የኮረና ቫይረስ ተጓዳኝ በሽታ ያለባቸውን ሰዎች ጤና በማወክ ህይወታቸው እንዲያልፍ የሚያደርግ ወረርሽኝ ነው፡፡ በመሆኑም ኤችአይቪ/ኤድስ በደማቸው የሚገኝ ወገኖች ያለምንም ቅድመ ሁኔታ እንዲሁም በኮረና ወረርሽኝ ስጋት ሳይደናገጡ በአቅራቢያቸው ወደሚገኝ የጤና ተቋማት በማምራት የፀረ- ኤችአይቪ መድሃኒታቸውን በመውሰድ በህክምና ባለሙያዎች በተሰጣቸው መመሪያ መሰረት መድሃኒታቸውን ወስደው ራሳቸውን ከኮረና ቫይረስና ከሌሎች ተጓዳኝ በሽታዎች መጠበቅ አለባቸው፡፡
በአገራችን የኤችአይቪ/ኤድስ ስርጭት ምጣኔ 0." data-share-imageurl="">