የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭት ከኮቪድ ወረርሽኝ ጋር ተዳምሮ እንዳይስፋፋ መረባረብ ያስፈልጋል - የጤና ሚኒስቴር

የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭት ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር ተዳምሮ እንዳይስፋፋ የሁሉም አካላት ርብርብ እንደሚያስፈልግ የጤና ሚኒስቴር አሳሰበ። ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ሰዎች በኮቪድ ከተያዙ ሕመሙን መቋቋም ስለሚያዳግታቸው የመከላከሉ ስራ በከፍተኛ ሁኔታ መጠናከር እንዳለበትም ተገልጿል።
የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል የሚረዱ ተግባራት እየተከናወኑ ቢሆንም ዓለም አቀፉ የኮሮና ወረርሽኝ ጥረቱን እየተገዳደረው መሆኑን የፌዴራል ኤች.አይ.ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጽህፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጽጌረዳ ክፍሌ ተናግረዋል፡፡
 
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ኮቪድ-19 በተከሰተባቸው የመጀመሪያዎቹ ወራት የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ሕሙማን የሕክምና ክትትል መቀዛቀዝ አሳይቶ እንደነበር አስታውሰዋል።
ይህን ተከትሎ ታማሚዎቹ ክትትላቸውን በስልክ ጭምር እንዲያደርጉ በተሰሩ ስራዎች መሻሻሎች እየታዩ መሆናቸውን ገልፀዋል። ቫይረሱ በደማቸው ያለባቸው ማኅበራት ጥምረት ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን አለሙ በበኩላቸው ኤች.አይ.ቪ ቫይረስ ከተከሰተ ጀምሮ በሽታውን በመከላከል እንዲሁም እንክብካቤና ድጋፍ በማድረግ ረገድ ቫይረሱ በደማቸው ውስጥ የሚገኝ ወገኖች ዋነኛ ተዋናዮች እንደነበሩ ጠቅሰዋል።መገለልና መድሎን በመቀነስ ረገድም የማይተካ ሚና እንደነበራቸው አስታውሰው፤ አሁንም ኅብረተሰቡ ራሱን ከኮቪድ እንዲጠብቅ ለማድረግ ተቀናጅተው እየሰሩ መሆኑን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
Source:EBC
Share it now!
የኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ስርጭት ከኮቪድ-19 ወረርሽኝ ጋር ተዳምሮ እንዳይስፋፋ የሁሉም አካላት ርብርብ እንደሚያስፈልግ የጤና ሚኒስቴር አሳሰበ። ቫይረሱ በደማቸው የሚገኝ ሰዎች በኮቪድ ከተያዙ ሕመሙን መቋቋም ስለሚያዳግታቸው የመከላከሉ ስራ በከፍተኛ ሁኔታ መጠናከር እንዳለበትም ተገልጿል።
የበሽታውን ስርጭት ለመከላከል የሚረዱ ተግባራት እየተከናወኑ ቢሆንም ዓለም አቀፉ የኮሮና ወረርሽኝ ጥረቱን እየተገዳደረው መሆኑን የፌዴራል ኤች." data-share-imageurl="">