መቅድም ኢትዮጵያ ብሔራዊ ማህበር USAID Family Focused HIV Prevention, Care and Treatment Services in Adiss Ababa City የተሰኘ ፕሮጀክት መጀመርን በማስመልከተ ከቦርድ አባላት፤ ባለድርሻ አካላትና አጋር ድርጅቶች ጋር ዎርክሾፕ አካሄደ፡፡

መቅድም ኢትዮጵያ ብሔራዊ ማህበር ለቀጣይ 3 ዓመታት የሚተገበረውን ከአሜሪካን ህዝብ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ “USAID Family Focused HIV Prevention, Care and Treatment Services in Adiss Ababa City” የተሰኘ ፕሮጀክትመጀመርን በማስመልከት በቢሾፍቱ እና አዲስ አበባ ከተማ ሁለት ዎርክሾፖችን አካሄደ፡፡

በቢሾፍቱ ከተማ በታህሳስ 17 2013 ዓ.ም በተካሄደው ወርክሾፕ  ከአ.አ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ፤ አ.አ ከተማ ኤች አይቪ ኤዲስ መከላከያና መቆጣጠሪያ፣ የአ.አ ከተማ አስተዳደር የህጻናት እና ወጣቶች ቢሮ፣ የአ.አ ከተማ አስተዳደር  የገንዘብ እና ኢኮኖሚ ቢሮ፣ፕሮግራሙን ተግባራዊ የሚያደረጉ አጋር ድርጅቶች ተወካዮች፣የሚመለከታቸዉ የመንግስት ባለስልጣናት እና ኢንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸዉ እንግዶች በተገኙበት ወርክሾፕ ተካሂዷል ፡፡

 በእለቱም ህይወታቸውን በኤችአይቪ ኤድስ ምክንያት ላጡ ወገኖቻችንን የህሊና ጸሎት የተደረገ ሲሆን USAID Family Focused HIV Prevention, Care and Treatment Services in Adiss Ababa City” ፐሮጀክትን ግብና እቅድ በፕሮጀክቱ ዋና አስተባበሪ (Chief of Party) ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ በእለቱም ከተሳታፊ እንግዶች እና ጥሪ ከተደረገላቸው የመንግስት ተወካዩች ላነሱዋቸው ጥያቆዎች ምላሽና ማብራራሪያ የተሰጠ ሲሆን ከተሳታፊዎችም  ሰፊ ግብዓት ለማሰባሰብ ተችሏል፡፡

በተያያዘም ጥር 9፣2013 ዓ.ም በሰሜን ሆቴል ከቦርድ አባላትና አጋር ድርጅቶች ጋር ተመሳሳይ ዎርክሾፕ  አካሂዷል፡፡ ይህ ወርክሾፕ ከቢሾፍቱ ቀጥሎ 2ኛዉ ሲሆን  በኮቪዲ-19 ምክንያት በወርክሾፑ የሚገኙትን ቁጥር ለመቀነስ ታሳቢ ባደረገ መልኩ የተተገበረ ነው፡፡

 በዚህም  ድርጅቱ   የ3 ዓመት USAID Family Focused HIV Prevention, Care and Treatment Services in Adiss Ababa City” ፕሮጀክት ስራ ውጤታማ ለማድረግ የሚያስችሉ ልዩ ልዩ ግብዓቶችን ከተሳታፊ አካላት ለማሰባሰብና ፐሮጀክቱንም ለማስተዋወቅ ተችሏል፡፡  በእለቱም ከዚህ በፊት በመቅድም ኢትዮጵያ ብሔራዊ ማህበር ውስጥ በቦርድ አባልነት ጉልህ አስተዋጽኦ የነበራቸውን አቶ ጋሻው መንግስቱ ህልፈት ምክንያት በማድረግ የህሊና ጸሎት የተደረገ ሲሆን በመቀጠል  ስለ ፐሮጀክቱም አጠቃላይ  እቅድና አተገባበር ሰፊ ገለጸ በአቶ አብይ አለማየሁ የፕሮጀክቱ ቺፍ ኦፍ ፓርቲ ቀርቦ ከተሳታፊ አካላት ጋር ሰፊ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

በዝግጅቱ ላይ የተገኙት የቦርድ አባላት፤ የአጋር ድርጀቶች ተወካዩች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶችም መቅድም ኢትዮጵያ ብሔራዊ ማህበር አስከዛሬ የነበረውን አበርክቶ እና ተግባራዊ ስራ አስታውሰው አሁን የተቀበለውን ይህንን ፐሮጀክት በከፍተኛ ስኬት እንዲተገብርና የታሰበውን ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ሊያደርግ የሚያስችለውን ሰፊ ስራ ለማሳካት ያግዛሉ ያሏቸውን አስተያየቶችና ምክሮችን አጋርተዋል፡፡  በተለይም አሁን ያለውን የመቅድም ኢትዮጵያ ብሔራዊ ማህበር አጠቃላይ አደረጃጀትና አሰራር ለማስቀጠልና በስሩ የሚሰሩ ሌሎች ድርጅቶችንም በሚገባ ለመምራት፤ ለመደገፍና ለመከታተል እንዲችል እየተዘጋጀ በሚገኘው ስትራቴጂ መነሻነት የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ከመቼውም በላይ በትኩረት በመያዝ ፈጠራና ቴክኖሎጂን በሚገባ በመጠቀም ስራዎችን ለመስራት ሰፊ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡

በተያያዘም ቦርዱ እና ሌሎች ባለድርሻ አካላትም በሚገባ ሚናቸውን እንዲወጡ የሚያሰችሉ ቅድመ ዝግጅቶችም እንዲደረጉ ጥሪ ቀርቧል፡፡ በመጨረሻም የተጀመረውን የ3 USAID Family Focused HIV Prevention, Care and Treatment Services in Adiss Ababa City” ፕሮጀክትን በታሰበው መልኩ ወደ ውጤት ለመቀየር እንዲቻል ሁሉም የድርሻውን እንዲወጣ በመጠቆም ና ለመቅድም ኢትዮጵያ ብሔራዊ ማህበር ቀጣይ ስኬት መልካሙን በመመኘት ወርክሾፑ ተጠናቋል፡፡

Share it now!
መቅድም ኢትዮጵያ ብሔራዊ ማህበር ለቀጣይ 3 ዓመታት የሚተገበረውን ከአሜሪካን ህዝብ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ “USAID Family Focused HIV Prevention, Care and Treatment Services in Adiss Ababa City” የተሰኘ ፕሮጀክትመጀመርን በማስመልከት በቢሾፍቱ እና አዲስ አበባ ከተማ ሁለት ዎርክሾፖችን አካሄደ፡፡

በቢሾፍቱ ከተማ በታህሳስ 17 2013 ዓ." data-share-imageurl="">