በመቅድም ኢትዮጵያ ብሔራዊ ማህበር አስተባባሪነት የ Prevention-Parenting for Lifelong Health/SINOVUYO ሪፍሬሸር ስልጠና ተካሄደ

በመቅድም ኢትዮጵያ ብሔራዊ ማህበር ዋናው ቢሮ አስተባባሪነት  ከዚህ በፊት በ Clowns Without Borders South Africa  (CWBSA) የ SINOVYUO (parenting lifelong health for both boys and girls)  ስልጠና ለወሰዱ  14 አሰልጣኞች (Facilitators) የሪፍሬሸር ስልጠና ከ ጥር 18- 19 , 2013 ዓ.ም ለሁለት ቀናት በአሰልጣኝ  Euni Motsa አስተባባሪነት ከደቡብ አፍሪካ  በበይነ መረብ ተሰጥቷል፡፡ በስልጠናውም ላይ ከ Maedot Childern and Women Focused Development (Maedot), Future Hope Integrated Development(FHIDO) , Love for Children and Family Development (LCFD), Common Vision Development Association (CVDA) , Mahbere Hiwot for Social Development (MSD) እና Mekdim Ethiopia National Association ( MENA )Addis Ababa Branch) የተወጣጡ አሰልጣኞች (Facilitators) ተካፍለዋል ፡፡

 የ Parenting for Lifelong Health/SINOVUYO ስልጠና በዋናነት በወላጆች ወይም አሳዳጊዎችና ልጆች መካከል ያለውን ቅርርብና ግንኙነት ለማዳበር፤ ወላጆች ልጆችን ለማሳደግ ያሉ አማራጮችን ለማስገንዘብና በወላጆችና በታዳጊዎች የግንዛቤ እጥረት ኤችአይቪን ጨምሮ ሌሎች አሉታዊ የጤና ችግሮችን ለመከላከል፤ ታዳጊዎችና ወጣቶች የኤችአይቪ ኤድስ ተጋላጭ የሚያደርጉዋቸው ሁኔታዎች ለመቀነስ ታሳቢ ባደረገ መልኩ የተዘጋጀ ስልጠና ነው፡፡ ስልጠናውም 14 ክፍሎች ላይ በዋናነት ያተኮረ  ሲሆን እነዚህም መርሃ ግብሩን ማስተዋወቅ እና የተሳታፊ ግቦችን ትርጓሜ ማስቀመጥ ፤ በአብሮነት ቆይታ ወቅት መልካም ግንኙነትን ማዳበር ፤ እርስ በእርስ መሞጋገስ ፤ ስለ ስሜቶች መነጋገር ፤ ስንናደድ ምን እናደርጋለን? ፤  ችግር አፈታት፦ እሳቱን ማጥፋት ፤  የቁጠባ ተነሳሽነት እና በገንዘባችን በጀት መመደብ ፤ ችግሮችን ያለግጭት መፍታት  ፤ ሕግጋትን እና እለታዊ ተግባራትን  ገንዘብ የማግኛ መንገዶች ፤  በማህበረሰብ እና በግንኙነቶች ውስጥ የተጠበቀ ደህንነት ፤ የቤተሰብ የቁጠባ እቅድ ማውጣት ለድንገተኛ ሁኔታ ምላሽ መሥጠት እና የድጋፍ ክበቡን ማስፋት ያካተተ ነው፡፡

በተለይም በዚህ የሪፍሬሸር ስልጠና በዋናነንት አሰልጣኞች (Facilitators) ከዚህ በፊት የወሰዱትን ስልጠና ታሳቢ በማድረግ ከኮቪድ 19 ወረርሽኝ መከሰት ጋር ተያይዞ የተቋረጠውን የተግባር ስልጠና ለማስቀጠል እንዲቻል  በፕሮግራሙ ይዘት ፣ ዘዴ ፣ አተገባበር እና የክህሎት ጋር ተያይዞ ያሉ ክፍተቶችን ለመለየትና ትግበራውን ለማስቀጠል እንዲቻል ዝግጁነታቸውን ለመገምገም እና ለመደገፍ ብሎም  ያላቸውን ወቅታዊ የማሰልጠን አቅምና ተነሳሽነት ለመጨመር ታሳቢ ያደረገ ነው፡፡ በስልጠናው ቆይታ አሰልጣኞች (Facilitators) ልዩ ልዩ ተግባራትን ና እንቅስቃሴዎችን በስኬት አጠናቀዋል፡፡

አሰልጣኞች (Facilitators) በተመደቡበት ቦታ ከማህበረሰቡ ለተወጣጡ ወላጆች፤ አፍላ ወንዶችና ሴቶች ልጆች በጋራ በትምህርት ተቋማትና ከትምህርት ተቋማትም ውጪ እንደ አመቺነቱ  ስልጠናዎችን የሚሰጡ ሲሆን የማስልጠን ተግባሮቻቸውንም በመመዘን እውቅና የሚሰጣቸው ይሆናል፡፡፡ ይህ ስልጠና  በመቅድም ኢትዮጵያ ብሔራዊ ማህበር አስተባባሪነት በ USAID የገንዘብ ድጋፍና በFHI-360 የቴክኒካል ድጋፍ በቅንጅት የተሰጠ ነው፡፡፡

 

 

 

Share it now!
በመቅድም ኢትዮጵያ ብሔራዊ ማህበር ዋናው ቢሮ አስተባባሪነት  ከዚህ በፊት በ Clowns Without Borders South Africa  (CWBSA) የ SINOVYUO (parenting lifelong health for both boys and girls)  ስልጠና ለወሰዱ  14 አሰልጣኞች (Facilitators) የሪፍሬሸር ስልጠና ከ ጥር 18- 19 , 2013 ዓ." data-share-imageurl="">