መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን ቤተሰብ ተኮር ኤች አይቪን የመከላከል እንክብካቤና ህክምና (USAID Family Focused HIV Prevention, Care and Treatment Services in Adiss Ababa City) ፕሮግራም የመጀመሪያ ሩብ አመት አፈጻጸም የግምገማ ዎርክሾፕ ፈጻሚ አጋር ድርጅቶች በተገኙበት አካሄደ፡፡

መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን ለቀጣይ 3 ዓመታት የሚተገበረውን ከአሜሪካን ህዝብ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ “USAID Family Focused HIV Prevention, Care and Treatment Services in Addis Ababa City” የተሰኘ ፕሮጀክት የመጀመረያ ሩብ አመት እቅድ  አፈጻጸምን በማስመልከትከ ከ ፕሮግራሙ ፈጻሚ ድርጅቶች (Local Implementing Partner ) ጋር በቢሾፍቱ ከተማ የ2 ቀናት ዎርክሾፕ አካሄደ ፡፡

በቢሾፍቱ ከተማ ጥር 12 እና 13 2013 ዓ.ም በተካሄደው ወርክሾፕ ከሁሉም ፕሮጀክቱ ፈጻሚ ድርጅቶች  የመጡ ሃላፊዎችና ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተገኝተዋል፡፡

ወርክሾፑ በዋናነት የመጀመሪያውን ሩብ ዓመት አፈጻጸም መነሻ በማድረግ በቀጣይ የሚሰሩ ስራዎችን በአግባብና በትብብር ለመስራት እና አጥጋቢ ውጤት ለማምጣት ታሳቢ ያደረገ ሰሆን በዚህም ሁሉም ፈጻሚ አጋር ድርጅቶች ወጥነት ያለውና ተግባራዊ ስራን ለመስራት የሚያግዙ ልምድ ልውውጦችና የጋራ እቅዶችን ለማውጣት አላማው ያደረገ ነው፡፡

በእለቱም ከመቅድም ኢትዩጵያ የገንዘብ ድጋፍ በማግኘት ፕሮጀክቱን እየፈጸሙ ያሉት ዘጠኝ (9)  ፈጻሚ ድርጅቶች ማለትም ከ Beza Posterity Development Organization(BPDO)፤ Faya Integrated Development Organization(FIDO) ፤ Maedot Children and Women Focused Development (Maedot), Future Hope Integrated Development(FHIDO) ,Love for Children and Family Development (LCFD)፤ Common Vision Development Association (CVDA)፤  Mahbere Hiwot for Social Development (MSD) እና Mekdim Ethiopia National Association ( MENA )Addis Ababa Branch) እና Love In Action Ethiopia (LIAE) በ ፕሮግራሙ የመጀመሪያ ሩብ ዓመት አፈጻጸም ሪፖርታቸውን አቅርበዋል፡፡ በቀረቡት ሪፖርቶችም ላይ ጥያቄና ግብረ መልስ እንዲሁም የልምምድ ልውውጦችም ተደርገዋል፡፡

በዚህም በመጀመሪያው ሩብ ዓመት በፕሮግራሙ አማካኝነት 1157 ሰዎች የኤች አይቪ ኤድስ ምርመራ የተደረገላቸው ሲሆን 92 ሰዎች በደማቸው ውስጥ ኤች አይቪ ኤድስ መገኘቱ ታውቋል፡፡ በዚህም ተመርምረው ኤች አይቪ በደማቸው ከተገኘባቸው 92 ሰዎች ውስጥ 89 ሰዎች የጸረ ኤች አይቪ መድሃኒት እንዲጀምሩ ወደ ጤና ተቋማት ለማስተሳሰር ተችሏል፡፡ በፕሮግራሙ  አጠቃላይ አፈጻጸም ላይም ውይይት ተደርጓል፡፡

በተለይም ከመረጃ ጥራት ጋር ተያይዞ የተገኙትን ግኝቶች መሰረት በማድረግ ጊዜውን የጠበቀ ሪፖርትን ለመንግስትና ሌሎች ባለድርሻ አካላትን መላክን፤መረጃና በአግባቡና ደህንነቱ በተጠበቀ መልኩ ማስቀመጥን፤ ተከታታይነት ያላቸውን የመረጃ ጥራት ማሻሻያ ስራዎችን መስራትን፤ የኤሌክትሮኒክስ መረጃ መመዝገቢያ (UDS/CommCare) በአግባብ መጠቀምን እና ኤች አይቪ ምርመራ ተደርጎላቸው ለመድሃኒት ቁርኝት የተላኩትን ደንበኞች መረጃ በአግባቡ ማስቀመጥ እና መከታተል ጋር ተያያዞ ያሉ ክፍተቶችን በሰፊው በመወያየት ለቀጣይ የተሻለ አፈጻጸም አቅጣጫ ተሰጥቷል፡፡

 

በተያያዘም ከፋይንስና ግራንት ጋር የተያያዙ ጉዳዩችን ለማጥራት ገለጻ የተደረገ ሲሆን ይህም በጀትን በአግባቡ ከመጠቀም ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ጥያቄዎች ግልጽ ለማድረግ ያስቻለ ነበር፡፡ በተመሳሳይ በፕሮጀክቱ አፈጻጸም ወቅት የሚስተዋሉትን የዳታ ጥራትና ተያያዥ ጉዳዩችን  በተመለከተም መሰል ገለጻ እና የግንዛቤ ስራዎችም ተደርገዋል፡፡

በዚህ ዎርክሾፕ የፕሮግራሙ አሁናዊ አጠቃላይ ሁኔታ ላይ ገለጻ የተደረገ ሲሆን በቀጣይ በእቀድ መሰረት የተሻለ ስራዎችና አፈጻጸሞችን ለማሰመዝገብም ሁሉም አጋር ድርጅቶች (Local Implementing Partners) በከፍተኛ ርብርብ መስራት አንዳለባቸው ከስምምነትም የተደረሰበት ነበር፡፡ በዚህም መነሻነት የቀጣይ የእቅድ አፈጻጸምን የተሳካ ለማድረግ የሚያስችል የአክሽን ፕላን በጋራ የተዘጋጀ ሲሆን ይህም ወጥነት ያለውና የተናበበ አፈጻጸም እንዲኖር ያግዛል ተብሎ ታምኖበታል፡፡

በመጨረሻም በተሳታፊዎች፤ የቴክኒካል ድጋፍ ሰጪ አካላት (Project Hope and Accelerating Support to Advanced Local Partner (ASAP) ) እና በተጋባዥ እንግዶች ለቀጣይ የተሻለ አፈጻጸም ያግዛሉ ተብሎ የታመነባቸው ዘርፈ ብዙ ሃሳቦችና አስተያየቶች የተሰበሰቡ ሲሆን ይህም ሁሉም ባለድርሻ አካላት ያለባቸውን ሃላፊነት በመረዳት እና ከሁሉም ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት ለመስራት ሁሉንም እድሎች ለመጠቀም እንዲችሉም መልዕክት ያስቻለ ነበር፡፡

Share it now!
መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን ለቀጣይ 3 ዓመታት የሚተገበረውን ከአሜሪካን ህዝብ በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ “USAID Family Focused HIV Prevention, Care and Treatment Services in Addis Ababa City” የተሰኘ ፕሮጀክት የመጀመረያ ሩብ አመት እቅድ  አፈጻጸምን በማስመልከትከ ከ ፕሮግራሙ ፈጻሚ ድርጅቶች (Local Implementing Partner ) ጋር በቢሾፍቱ ከተማ የ2 ቀናት ዎርክሾፕ አካሄደ ፡፡

በቢሾፍቱ ከተማ ጥር 12 እና 13 2013 ዓ." data-share-imageurl="">