ኤችአይቪን በመከላከል ረገድ ትልቅ ውጤት የሚያስገኝ የአፍሪካ ጥናት ይፋ ሆኗል

በዓለም ዙሪያ በኤችአይቪ ከተያዙ ሰዎች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው፡፡ በአህጉራችን አፍሪካ በሁለቱም ፆታዎች ከሚያዙ ሰዎች በተጨማሪ በተለይም በምስራቅ እና የደቡብ አፍሪካ ቀጠናዎች በቫይረሱ የሚጠቁ ሴቶች በአምስት እና በሰባት አመታት ከወንዶች ቀድመው እንደሚያዙ የተለያዩ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ የኤችአይቪ ቫይረስን በአሁጉሪቱ ለመከላከል ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች ለረዥም ጊዚያት መተግበራቸው የሚታወቅ ሲሆን፤ ቫይረሱን ቀድሞ ለመከላከል በሚደረገው ጥረትም የተለያዩ የመድሃኒት አይነቶች ጥቅም ላይ ሲውሉ መቆየታቸው የሚታወቅ ነው፡፡
በተለይም የቅድመ-ተጋላጭነት መከላከያ (PrEP) ጋር ተያይዞ የተለያዩ የመድሃኒት አይነቶች ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ ከእነዚህ ወስጥ በስፋት የሚታወቀው መድሃኒት (ትሩቫዳ) Truvada የተሰኘው የኤችአይቪ መከላከያ መድሃኒት አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ ይህ መድሃኒት በሁለት ጥምር የፀረ-ቫይረስ (antiretroviral) መከላከያ መድሃኒቶች አማካኝነት የሚሰጥ ሲሆን አነሱም tenofovir እና emtricitabine በመባል ይታወቃሉ፡፡ ይህ መድሃኒት ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ያለማቋረጥ የሚወስዱት ከሆነ በቫይረሱ ያለመያዝ እድላቸውን 99% ስኬታማ ቢያደርገውም ከዋጋ ውድነቱ ጋር ተያይዞ ብዙ ሰዎች መድሃኒቱን በየቀኑ መውሰድ እጅግ አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል፡፡ በተለይም በአፍሪካ የሚገኙ ብዙ ሰዎች ከገቢ ማነስ ጋር ተያይዞ መድሃኒቱን የማግኝት እድላቸው እጅግ የጠበበ ነው፡፡
ታዲያ ይህን የተመለከቱ የአፍሪካ የቁርጥ ቀን ልጆች በቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች በረዥም የቀናት ልዩነት ውስጥ ሊወስዱት የሚችሉት እና ውጤታማነቱ በሚገባ የተረጋገጠ የኤችአይቪ መከላከያ መድሃኒት ይፋ አድርገዋል፡፡ በአፍሪካ በቅርቡ ምስረታውን ካደረገው የኤችአይቪ መከላከያ ሙከራዎች አውታርመረብ (HPTN) የተወጣጡ ሳይንቲስቶች እንዳስታወቁት በአዲሱ ጥናት መሰረት በ8 ሳምንታት ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ የሚወሰደው አዲሱ ካቤትግራቪር (cabotegravir) መድሃኒት እጅግ ውድ እና በየቀኑ ሊወሰዱ ከሚገባቸው እንደ ትሩቫዳ (Truvada) ካሉ የቅድመ-ተጋላጭነት መከላከያ መድሃኒቶች አንፃር በእጅጉ ተሽሎ የቀረበ መሆኑን ይፋ አድርገዋል፡፡
HPTN 084 የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ የሳይንቲስቶች ጥናት በ8 ሳምንታት ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ በመርፌ የሚወሰደውን ካቤትግራቬር (cabotegravir) መድሃኒት ከእውቁ የትሩቫዳ መከላከያ መድሃኒት ጋር ለማነፃፀር የቻለ ሲሆን በውጤቱም እጅግ ተቀራራቢ ግኝት ከጥናቱ ሊገኝ መቻሉን የምርምሩ ተሳታፊ ኢና እስኮዛና ተናግረዋል፡፡ በዚህ ጥናት 3,200 የሚጠጉ በቫይረሱ ያልተያዙ ሲቶች የተሳተፉ ሲሆን በሰባት የአፍሪካ ሃገራት የምርምር ጣቢያዎች ለሶስት አመት ያክል ክትትል ሲደረግላቸው መቆዩቱም ተነግሯል፡፡ ተመራማሪዎች ጥናቱን በሁለት መንገድ በመምራት በቅድሚያ ካቤትግራቪር መድሃኒትን ከትሩቫዳ placebos ጋር ለተሳታፊዎች የሰጡ ሲሆን በሁለተኛው ሂደትም የትሩቫዳ መድሃኒትን ከካቤትግራቪር placebos ጋር በማድረግ ጥናቱን አካሂደዋል፡፡
የHPTN ሳይንቲስቶች በእጃቸው ላይ ካለው 50 ጥናቶች መካከል አንዱ በሆነው በዚህ ምርምር የተገኘው ውጤት እንደሚያሳየው በጥናቱ ከተሳተፉ 3,200 ሰዎች ማካከል በቫይረሱ የተያዙት 38 ወይም 1% የሚሆኑት ብቻ ሲሆኑ፤ ይህም ሁለቱም መደሃኒቶች ቫይረሱን በመካለከል ሂደት ውጤታማ መሆናቸውን የሚያመለክት ነው፡፡ በጥናቱ ሂደት በቫይረሱ የተያዙት 34 ሴቶች የትሩቫዳ መድሃኒትን ሲወስዱ በ1.79% በቫይረሱ የመያዝ እድል ኖሯቸው የተገኘ ሲሆን፤ የካቤትግራቪር መድሃኒትን የተጠቀሙ 4 ሴቶች ግን በቫይረሱ የመያዝ እድላቸው 0.21% ብቻ እንደነበር በጥናቱ ለማየት ተችሏል፡፡ ይህ አውነትም በብዙ ሳምንታት መካከል ሊወሰድ የሚችለው የካቤትግራቪር መድሃኒት ትሩቫዳ ከሚሰጠው ጥቅም ይልቅ እጅግ የተሻለ መሆኑን የሚያመልክት ነው፡፡
በዚህ ጥናት መሰረት የካቤትግራቪር መድሃኒት ለአፍሪካውያን ጥቅም ላይ የሚውልበትን ሂደት ለማስጀመር ተጨማሪ ስራዎች እንዲሚቀጥሉ እና በአጭር ጊዜ ውስጥ ለአገልግሎት እንደሚበቃ የሚስረዱት በጆሃንስበርግ የዊትዋተርዝራንድ ዩኒቨርስቲ ተመራማሪ ዶ/ር ሺኔድ ዲሌኒ ኤችአይቪን በመከላከል ረገድ የመሰረት ድንገይ የሚጥል ውጤት መገኘቱን ይናገራሉ፡፡
ምንጭ፡ FDRE Technology and Innovation Institute, The Conversation እና CDC

Share it now!
በዓለም ዙሪያ በኤችአይቪ ከተያዙ ሰዎች መካከል ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ሴቶች ናቸው፡፡ በአህጉራችን አፍሪካ በሁለቱም ፆታዎች ከሚያዙ ሰዎች በተጨማሪ በተለይም በምስራቅ እና የደቡብ አፍሪካ ቀጠናዎች በቫይረሱ የሚጠቁ ሴቶች በአምስት እና በሰባት አመታት ከወንዶች ቀድመው እንደሚያዙ የተለያዩ ጥናቶች ይጠቁማሉ፡፡ የኤችአይቪ ቫይረስን በአሁጉሪቱ ለመከላከል ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች ለረዥም ጊዚያት መተግበራቸው የሚታወቅ ሲሆን፤ ቫይረሱን ቀድሞ ለመከላከል በሚደረገው ጥረትም የተለያዩ የመድሃኒት አይነቶች ጥቅም ላይ ሲውሉ መቆየታቸው የሚታወቅ ነው፡፡
በተለይም የቅድመ-ተጋላጭነት መከላከያ (PrEP) ጋር ተያይዞ የተለያዩ የመድሃኒት አይነቶች ጥቅም ላይ ይውላሉ፡፡ ከእነዚህ ወስጥ በስፋት የሚታወቀው መድሃኒት (ትሩቫዳ) Truvada የተሰኘው የኤችአይቪ መከላከያ መድሃኒት አንዱና ዋነኛው ነው፡፡ ይህ መድሃኒት በሁለት ጥምር የፀረ-ቫይረስ (antiretroviral) መከላከያ መድሃኒቶች አማካኝነት የሚሰጥ ሲሆን አነሱም tenofovir እና emtricitabine በመባል ይታወቃሉ፡፡ ይህ መድሃኒት ለቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች ያለማቋረጥ የሚወስዱት ከሆነ በቫይረሱ ያለመያዝ እድላቸውን 99% ስኬታማ ቢያደርገውም ከዋጋ ውድነቱ ጋር ተያይዞ ብዙ ሰዎች መድሃኒቱን በየቀኑ መውሰድ እጅግ አስቸጋሪ ይሆንባቸዋል፡፡ በተለይም በአፍሪካ የሚገኙ ብዙ ሰዎች ከገቢ ማነስ ጋር ተያይዞ መድሃኒቱን የማግኝት እድላቸው እጅግ የጠበበ ነው፡፡
ታዲያ ይህን የተመለከቱ የአፍሪካ የቁርጥ ቀን ልጆች በቫይረሱ ተጋላጭ የሆኑ ሰዎች በረዥም የቀናት ልዩነት ውስጥ ሊወስዱት የሚችሉት እና ውጤታማነቱ በሚገባ የተረጋገጠ የኤችአይቪ መከላከያ መድሃኒት ይፋ አድርገዋል፡፡ በአፍሪካ በቅርቡ ምስረታውን ካደረገው የኤችአይቪ መከላከያ ሙከራዎች አውታርመረብ (HPTN) የተወጣጡ ሳይንቲስቶች እንዳስታወቁት በአዲሱ ጥናት መሰረት በ8 ሳምንታት ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ የሚወሰደው አዲሱ ካቤትግራቪር (cabotegravir) መድሃኒት እጅግ ውድ እና በየቀኑ ሊወሰዱ ከሚገባቸው እንደ ትሩቫዳ (Truvada) ካሉ የቅድመ-ተጋላጭነት መከላከያ መድሃኒቶች አንፃር በእጅጉ ተሽሎ የቀረበ መሆኑን ይፋ አድርገዋል፡፡
HPTN 084 የሚል ስያሜ የተሰጠው ይህ የሳይንቲስቶች ጥናት በ8 ሳምንታት ውስጥ አንድ ጊዜ ብቻ በመርፌ የሚወሰደውን ካቤትግራቬር (cabotegravir) መድሃኒት ከእውቁ የትሩቫዳ መከላከያ መድሃኒት ጋር ለማነፃፀር የቻለ ሲሆን በውጤቱም እጅግ ተቀራራቢ ግኝት ከጥናቱ ሊገኝ መቻሉን የምርምሩ ተሳታፊ ኢና እስኮዛና ተናግረዋል፡፡ በዚህ ጥናት 3,200 የሚጠጉ በቫይረሱ ያልተያዙ ሲቶች የተሳተፉ ሲሆን በሰባት የአፍሪካ ሃገራት የምርምር ጣቢያዎች ለሶስት አመት ያክል ክትትል ሲደረግላቸው መቆዩቱም ተነግሯል፡፡ ተመራማሪዎች ጥናቱን በሁለት መንገድ በመምራት በቅድሚያ ካቤትግራቪር መድሃኒትን ከትሩቫዳ placebos ጋር ለተሳታፊዎች የሰጡ ሲሆን በሁለተኛው ሂደትም የትሩቫዳ መድሃኒትን ከካቤትግራቪር placebos ጋር በማድረግ ጥናቱን አካሂደዋል፡፡
የHPTN ሳይንቲስቶች በእጃቸው ላይ ካለው 50 ጥናቶች መካከል አንዱ በሆነው በዚህ ምርምር የተገኘው ውጤት እንደሚያሳየው በጥናቱ ከተሳተፉ 3,200 ሰዎች ማካከል በቫይረሱ የተያዙት 38 ወይም 1% የሚሆኑት ብቻ ሲሆኑ፤ ይህም ሁለቱም መደሃኒቶች ቫይረሱን በመካለከል ሂደት ውጤታማ መሆናቸውን የሚያመለክት ነው፡፡ በጥናቱ ሂደት በቫይረሱ የተያዙት 34 ሴቶች የትሩቫዳ መድሃኒትን ሲወስዱ በ1." data-share-imageurl="">