መቅድም ኢትዩጵያ ናሽናል አሶሴሽን ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር አለም አቀፍ ኤች አይቪ ኤድስ ቀንን በድምቀት አክብረዋል።
November 30, 2023 Comments Off on መቅድም ኢትዩጵያ ናሽናል አሶሴሽን ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ጋር በመተባበር አለም አቀፍ ኤች አይቪ ኤድስ ቀንን በድምቀት አክብረዋል። Uncategorized Mena Admin

በየአመቱ ዴሴምበር 01 የሚከበረውን የአለም አቀፍ ኤች አይቪ ኤድስ ቀን በዚህም አመት በአዲስ አበባ ከተማ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በፓናል ውይይት ተከብሮ ውሏል፡፡ በዚህ አመት “የማህበረሰብ መሪነት ለላቀ ለኤች አይቪ ኤድስ መከላከል” በሚል መሪ ቃል የተከበረ ሲሆን በእለቱም የአዲስ አበባ ጤና ቤሮ ም/ቢሮ ሃላፊ ወ/ሮ አንጋቱ መሃመድና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች፤ ከሁሉም ሴክተር ቢሮዎች የተጋበዙ ቢሮ ሃላፊዎች፤ የሁሉም ክፍለ ከተማ ጤና ቢሮ ሃላፍዎች፤ ኤችይቪ ኤድስ በደማቸው ከሚገኝባቸው ማህበራትና ጥምረቶች የተጋበዙ ተወካዮች፤ ከእድሮችና ሌሎች የማህበረሰብ አደረጃጀቶች የተወጣጡ የክብር እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ተከብሮ ውሏል፡፡
በእለቱም የመጡትን ሁሉን አቀፍ ለውጦች እውቅና መስጠት እንደተጠበቀ ሆኖ በተለይ ትኩረት የሚሹ የማህበረሰብ ክፍሎች ላይ ትኩረት አድርጎ መስራትና በተጨማሪም በትምህርት ቤቶችና ከባህል ባፈነገጡ አስተሳሰቦች ዙሪያም ተጨማሪ ርብርብ የሚጠይቁ የሁሉም ባለድርሻ አካላት የጋራ የቤት ስራዎች መሆናቸውም ተሰምሮበታል፡፡

About The Author