የሃይማኖት ተቋማት በኤችአይቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ የሚኖራቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ የተዘጋጀ ከፍተኛ የምክክር መድረክ ተካሄደ
March 21, 2024 Comments Off on የሃይማኖት ተቋማት በኤችአይቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ የሚኖራቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ የተዘጋጀ ከፍተኛ የምክክር መድረክ ተካሄደ Uncategorized Mena Admin

መቅድም ኢትዮጲያ ናሽናል አሶሴሽን ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጋር በመተባበር የተዘጋጀው የሃይማኖት ተቋማት በኤችአይቪ/ኤድስ መከላከልና መቆጣጠር ዙሪያ የሚኖራቸውን ተሳትፎ ለማሳደግ የተዘጋጀ ከፍተኛ የምክክር መድረክ የሃይማኖት አባቶች፤ የጤና ሚኒስትር ከፍተኛ ሃላፊዎች፤ የአሜሪካ መንግስት ተራድኦ ድርጅት ተወካዩች ፤ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶችና የሚዲያ ባለሙያዎች በተገኙበት ተካሂዷል፡፡
በዚህ በአይነቱ ልዩ በሆነና በጋራ ትብብር በተዘጋጀ የምክክር መደረክ ላይ የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ አባል የሃይማኖት ተቋማት አባቶች ሰፊ የግንዛቤ ማስጨበጥ ስራና ለመስራት የሚያስችል መልእክቶችን ለሃይማኖቱ ተከታዩች ያስተላለፉ ሲሆን በጤናው ዘርፈ ኤች አይቪ ኤድስን ለመቆጣጠር የሚደረገውን ሁሉን አቀፍ ጥረትም ተረድቶ በመደገፍ ዙሪያ ሰፊ ውይይትና ንቅናቄ የተፈጠረበትም ነበር፡፡ በጤና ዘርፍ ላለፉት 20 አመታት በቅንጅት በተሰሩ ስራዎች ሃገራዊ የኤች አይቪ የስርጭት ምጣኔ ለመቀነስ መቻሉን የተነሳ ሲሆን ነገር ግን አሁንም በአንዳንድ አካባቢዎች ስርጭቱ ከሀገራዊ ምጣኔ በላይ በመሆኑና አዲስ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በርካታ በመሆኑ ይህንን ለመቀልበስ የሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል በተለይም የሃይማኖት አባቶችንም ትኩረት እንደሚሻም ተጠቁሟል፡፡
በዚህ ከፍተኛ ሃገራዊ የምክክር መድረክ ላይ ሁሉም ባለድርሻ አካላት በቀጣይ ኤች አይቪ ኤድስ ምርመራ እና ህክምና ዙሪያ ያሉ የግንዛቤ ክፍተቶችን በቅንጅት ለመፍታት የሚያስችል መግባባት የተደረሰበትም ነው ፡፡ #MENA #IRCE

About The Author