ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃትን ለመከላከል በሚደረገው ሁሉ አቀፍ ጥረት መልካም ወንድነት ያለውን ሚና የሚዳስስ የምክክር ዎርክሾፕ ተካሄደ።
November 29, 2023 Comments Off on ጾታን መሰረት ያደረገ ጥቃትን ለመከላከል በሚደረገው ሁሉ አቀፍ ጥረት መልካም ወንድነት ያለውን ሚና የሚዳስስ የምክክር ዎርክሾፕ ተካሄደ። News Mena Admin

በመላው አለም ጾታን መሰረተ ያደረጉ ጥቃቶችን ለመከላከል የሚደረገውን ሁሉን አቀፍ ጥረት ለመዘከር በየአመቱ 16 ቀን ዘመቻ አካል የሆነው የመልካም ወንድነት ሚና የሚያነሳ ምክክር በመቅድም ኢትዩጵያ ናሽናል አሶሴሽን አዘጋጅነት ተካሂዷል፡፡ በዚህ ምክክር ዎርክሾፕ ላይ ከአዲስ አበባ ሴቶችና ማህበራዊ ቢሮ ፤ ጤና ቢሮ ከተወከሉ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች፤ ከመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ከሚገኙ መምህራን ና ከሃገር በቀል ፈጻሚ ድርጅቶች የተጋበዙ ተሳታፊዎች ተጋብዘዋል ፡፡ በዚህ ምክክር ላይ በአሜሪካ ህዝብና መንግስት ድጋፍ በመተግበር ላይ በሚገኘው ቤተሰብ አቀፍ የኤች አይቪ ኤድስ እንክብካቤና ድጋፍ አገልግሎት ፕሮግራም ተግባራት አካል የሆነውን ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን ለመከላከል የሚደረጉ ስራዎችን፤ በመከላከል ስራዎች ውስጥ የመልካም ወንዶችን ሚና ለማጎልበት አእድሜያቸው ከ 10_ 14 በትምህርት ቤቶች ውስጥ በመሰራት ላይ የሚሰሩ ስራዎችን ሚና ብሎም በአዲስ አበባ ከተማ ደረጃ ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን አሁናዊ ሁኔታና ቀጣይ የትኩረት ጉዳዩችን የሚዳስሱ ውይይቶች ተደርገዋል ፡፡
በዚህ አመት ጾታዊ ጥቃትን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት” መቼም ፤ የትም፤በምንም ሁኔታ ጾታዊ ጥቃትን ዝም አንበል “ በሚል መሪ ቃል በመከበር ላይ ነው ፡፡
መቅድም ኢትዩጵያ ናሽናል አሶሴሽን ኤች አይቪ ኤድስና ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶችን ለመከላከልና ለመቀነስ የሚደረገውን ዘርፈ ብዙ ጥረት ለመደገፍ በግንባር ቀድምትነት በመሰለፍ ከሁሉም መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት በመስራት ላይ ይገኛል፡ ፡

Tags
About The Author