መቅድም ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ ፡፡
መቅድም ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ስትራቴጂካዊ አጋርነታቸውን ይበልጥ ለማጠናከር ተስማሙ ፡፡
መቅድም ኢትዮጵያ ብሔራዊ ማህበር እና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ለበርካታ ዓመታት የቆየውን የጋራ ትብብር ወደ ተጠናከረ ዘርፈ-ብዙ ስትራቴጂካዊ አጋርነት ለማሸጋገር ያለመ ከፍተኛ የሥራ መሪዎች የምክክር መድረክ አካሂደዋል።
በጤናው ዘርፍ ያለውን የቴክኒክ ልምድ እና የሃይማኖት ተቋማትን መንፈሳዊ መሪነት ማቀናጀት ያለውን ፋይዳ በመገንዘብ በጋራ በመተግበር ላይ ከሚገኙት ፕሮግራሞች በተጨማሪ፤ ሁለቱም ተቋማት አዲስ ስትራቴጂካዊ መርሐ-ግብር ነድፈው ለመንቀሳቀስ ተስማምተዋል። ይህ ስምምነት ተቋማዊ ዘላቂነትን በማረጋገጥ የጤና ና የማህበራዊ አገልግሎቶችን ተደራሽነት ይበልጥ ለማስፋት እንዲሁም ከኤች.አይ.ቪ/ኤድስ ባለፈ ሰፊ የሕዝብ ጤና እና ማህበራዊ ድጋፍ ጉዳዮች ላይ በጋራ ለመስራት የሚያስችል ነው።
ይህም በሃይማኖት ተቋማት ጋር በቅንጅት የሚተገበሩ ማህበረሰብ-ተኮር የጤና አገልግሎቶች በኢትዮጵያ ብሔራዊ የጤና ሥርዓት ውስጥ ግንባር ቀደም የድጋፍ ምሰሶ ሆኖ እንዲቀጥል ያስችላል።
“ ኤች አይ ቪ በደማቸዉ የሚገኝባቸዉንና በኤድስ ምክንያት ችግር ያጋጠማቸዉን ወገኖች እናፍቅር! እንርዳ! እንንከባከብ“
ከመቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን ጋር አብረው ይስሩ፤ ለተጨማሪ መረጃዎች ገጻችንን ይከታተሉ።


