📢 ይፋዊ ማስታወቂያ፡ የድርጅታችንን አዲስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ስለማሳወቅ
September 1, 2025 Comments Off on 📢 ይፋዊ ማስታወቂያ፡ የድርጅታችንን አዲስ ዋና ስራ አስፈፃሚ ስለማሳወቅ Uncategorized Mena Admin

የመቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን ቦርድ አቶ መኮንን አለሙ አማኑን ዋና ስራ አስፈፃሚ አድርጎ መሾሙን በደስታ ይገልጻል።
አቶ መኮንን ባላቸው የዳበረ የአመራር ልምድ፣ ማህበረሰብን ያማከለ አገልግሎት ለመስጠት ባለው ቁርጠኝነት ድርጅታችን በመላው ኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ የኤችአይቪ መከላከል፣ እንክብካቤ እና ድጋፍ አገልግሎት የመስጠት ተልእኳችንን ለማሳደግ በምናደርገው ጥረት ትልቅ አቅም ሆነው ወደ ድርጅታችን አመራርነት ተቀላቅለዋል፡፡
በዚህም ወቅት ለመላው የድርጅታችን አባላት፣ ሰራተኞች፣ አጋሮች እና ደጋፊዎች በሙሉ ለቀጠለው ድጋፍና አብሮነት ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን። አሁንም ከአቶ መኮንን አመራር ጋር በመሆን ማህበረሰባንችን በማብቃት ለማገልገል እና ለሀገር አቀፍ የኤችአይቪ ምላሽ የበኩላችንን አስተዋፅኦ በማበርከት ረገድ ሰፊ ስራን በትብብር ለመስራትም በምናደርገው ሁሉን አቀፍ ጥረት ከጎናችን እንደምትሆኑም እናምናለን፡፡
ሁሉም ባለድርሻ አካላት አቶ መኮንን አለሙ አማኑን ወደ መቅድም ኢትዮጵያ ቤተሰብ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት መልካም ምኞታችሁን አንድትገልጹም በአክብሮት እንጋብዛለን።
በምናገለግላቸው ማህበረሰቦች ህይወት ላይ ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት እጅ ለእጅ ተያይዘን እንቀጥል።
ከአክብሮት ጋር፣
መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን (MENA)

About The Author