የ2025 የዓለም ኤድስ ቀን አውደ ጥናት በስኬት ተጠናቀቀ! 🤝🎗️
December 4, 2025 Comments Off on የ2025 የዓለም ኤድስ ቀን አውደ ጥናት በስኬት ተጠናቀቀ! 🤝🎗️ News Mena Admin

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ እና በመቅዲም ኢትዮጵያ ብሔራዊ ማህበር (MENA) ትብብር በሶራምባ ሆቴል ሲካሄድ የነበረው የ2025 የዓለም ኤድስ ቀን መታሰቢያ ዎርክሾፕ በከፍተኛ ስኬት ተጠናቋል።
በመድረኩ ላይ ከአዲስ አበባ ጤና ቢሮ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ከተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች፣ ከ ANNOPA+ እና ሌሎች የPLHIV associations የተወከሉ አመራሮች፣ እንዲሁም የመቅዲም ቦርድ አመራሮች፣ አባላት እና ሰራተኞች ተሳትፈዋል።
የውይይቱ ዋና ውጤት፡- ውይይቱ በተጋሩ ተሞክሮዎች እና በጠንካራ መንፈስ የታጀበ ነበር። ተሳታፊዎች በኤችአይቪ/ኤድስ ምላሽ ላይ የሚታዩ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና አዳዲስ አሰራሮችን (Innovative Approaches) በማጠናከር በጋራ ለመስራት ቃላቸውን አድሰዋል። በተለይም የሀገር ውስጥ አቅምን በማጎልበት የኤችአይቪ ምላሽን ዘላቂነት ለማረጋገጥ ስምምነት ላይ ተደርሷል።
“ተግዳሮቶችን በመቋቋም፣ የኤችአይቪ/ኤድስ ምላሽን ዘላቂነት እናረጋግጥ!

Tags
About The Author