መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ ለማሻሻል የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ አካሄደ
January 16, 2026 Comments Off on መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ ለማሻሻል የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ አካሄደ Uncategorized Mena Admin

መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ ለማሻሻል በተጀመረው ሂደት ውስጥ ወሳኝ ምዕራፍ የሆነውን የባለድርሻ አካላት የምክክር መድረክ አካሄዷል፡፡ ይህ የውይይት መድረክ ደንቡን ለማሻሻል በስራ አመራር ቦርድ የተሰየመው ኮሚቴ ፤ የአዲስ አበባ ቅርንጫፍ የጠቅላላ ጉባኤ ተወካዩች እና ከአባላትም የተካተቱበት ሲሆን፤ አሁን ያለውን ረቂቅ ደንብ ለመገምገም እና ይበልጥ ለማበልጸግ ያለመ የባለ ድርሻ አካላት የምክክር መድረክ አካሄደዋል።
የዚህ የደንብ ማሻሻያ ዋና ግብ የማህበሩ መተዳደሪያ ደንብ ሁሉንም አባላት ያሳተፉ፣ ግልጽነት ያላቸው እና አባላት ለማህበሩ አላማ መሳካት የሚያደርጉትን አስተዋጽኦ በይበልጥ እንዲያበረክቱ የሚያስችሉ ለማድረግ ነው ፡፡
የማህበሩን መተዳደሪያ ደንብ የማሻሻል ሂደቱ ቀጣይነት የሚኖረና በውይይቱ የተገኙ ገንቢ ሃሳቦችና አስተያየቶችን በማካተትም በቀጣይ ተጨማሪ ውይይትና ማሻሻያ የሚደረግበት ይሆናል ፡፡
መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን በዚህ ሂደት ላይ ሚናቸውን በመወጣት ላይ የሚገኙትን ሁሉንም ባለድርሻ አካላት ያመሰግናል፡፡

About The Author