የጎዳና ጎልማሶች  ኘሮጀክትእንቅስቃሴ በደሴ ከተማ አስተዳዳር ሃላፊዎች ተጎብኝቷል፡፡
July 19, 2023 Comments Off on የጎዳና ጎልማሶች  ኘሮጀክትእንቅስቃሴ በደሴ ከተማ አስተዳዳር ሃላፊዎች ተጎብኝቷል፡፡ Uncategorized Mena Admin

መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን ደሴ  ቅርንጫፍ  ከማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ጋር በጋራ በመሆን በመተግበር ላይ በሚገኘው   የጎዳና ጎልማሶች  ኘሮጀክት ስራ በደሴ ከተማ ከንቲባ  አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ እና የዘርፍ አመራሮች ተጎብኝቷል፡፡  መቅድም ደሴ ቅርንጫፍ የተረከባቸውን ወጣቶች ከሱስ እንዲያገግሙና ልዩ ልዩ ስልጠናዎችን በመውሰድ ወደ ስራ አለም የሚቀላቀሉብትን መንገድ ለማመቻቸት ባለፉት ወራት ከፍተኛ ስራ ያከናወን ሲሆን  የፕሮክክቱ አጠቃላይ ውጤትም ቀርቦ በጋራ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ይህም በከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ከፍትኛ እውቅና እና ምስጋናን ለማግኘት አስችሏል፡፡ በዚህም መነሻነት የከተማ አስተዳደሩ የሚያደርገውን ድጋፍ ይበልጥ ለማጠናከርና ለወጣቶቹ የስራ እድልን ለመፍጠር፤ ተጨማሪ የክህሎት ስልጠናዎችን ለማዘጋጅትና የበጀት ድጎማ ለማድረግም ቃል የገባ ሲሆን ወጣቶቹም ስለተደረገላቸው ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበው በቀጣይም ከተማ አስተዳዳሩ ቃል በገባው መሰረት ከደገፋቸው በስራ መስክ ላይ ውጤታም ስራ ሰርተው ማሳየት እንደሚችሉም አረጋግጠዋል፡፡

በመጨረሻም መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን ደሴ  ቅርንጫፍ   ከተማ አስተዳዳሩ ከፕሮጀክቱ ጅማሮ አንስቶ መጠለያዎችን በማመቻችትና ዘርፈ ብዙ ድጋፍ በመስጠት ላደረገው አስተዋጸኦ እና በቀጣይነትም እያሳየ ላለው ቁርጠኝነት ከፍተና ምስጋና አቅርቧል፡፡

ኑ በጋራ የወጣቶችን ህይወት በመቀየር ለጋራ ሃገር  ግ ንባታ እንስራ !

መቅድም ኢትዩጵያ ናስናል አሶሴሽን

About The Author