የጎዳና ጎልማሶች ኘሮጀክትእንቅስቃሴ በደሴ ከተማ አስተዳዳር ሃላፊዎች ተጎብኝቷል፡፡
መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን ደሴ ቅርንጫፍ ከማህበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር ጋር በጋራ በመሆን በመተግበር ላይ በሚገኘው የጎዳና ጎልማሶች ኘሮጀክት ስራ በደሴ ከተማ ከንቲባ አቶ ሳሙኤል ሞላልኝ እና የዘርፍ አመራሮች ተጎብኝቷል፡፡ መቅድም ደሴ ቅርንጫፍ የተረከባቸውን ወጣቶች ከሱስ እንዲያገግሙና ልዩ ልዩ ስልጠናዎችን በመውሰድ ወደ ስራ አለም የሚቀላቀሉብትን መንገድ ለማመቻቸት ባለፉት ወራት ከፍተኛ ስራ ያከናወን ሲሆን የፕሮክክቱ አጠቃላይ ውጤትም ቀርቦ በጋራ ውይይት ተደርጎበታል፡፡ ይህም በከተማ አስተዳደሩ አመራሮች ከፍትኛ እውቅና እና ምስጋናን ለማግኘት አስችሏል፡፡ በዚህም መነሻነት የከተማ አስተዳደሩ የሚያደርገውን ድጋፍ ይበልጥ ለማጠናከርና ለወጣቶቹ የስራ እድልን ለመፍጠር፤ ተጨማሪ የክህሎት ስልጠናዎችን ለማዘጋጅትና የበጀት ድጎማ ለማድረግም ቃል የገባ ሲሆን ወጣቶቹም ስለተደረገላቸው ድጋፍ ከፍተኛ ምስጋና አቅርበው በቀጣይም ከተማ አስተዳዳሩ ቃል በገባው መሰረት ከደገፋቸው በስራ መስክ ላይ ውጤታም ስራ ሰርተው ማሳየት እንደሚችሉም አረጋግጠዋል፡፡
በመጨረሻም መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን ደሴ ቅርንጫፍ ከተማ አስተዳዳሩ ከፕሮጀክቱ ጅማሮ አንስቶ መጠለያዎችን በማመቻችትና ዘርፈ ብዙ ድጋፍ በመስጠት ላደረገው አስተዋጸኦ እና በቀጣይነትም እያሳየ ላለው ቁርጠኝነት ከፍተና ምስጋና አቅርቧል፡፡
ኑ በጋራ የወጣቶችን ህይወት በመቀየር ለጋራ ሃገር ግ ንባታ እንስራ !
መቅድም ኢትዩጵያ ናስናል አሶሴሽን


