የሀዘን መግለጫ
የመቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን መስራች፣ አባል እና ዋና ስራ አስፈጻሚ በመሆን ከ30 አመታት በላይ በትጋት፣ በቁርጠኝነት እና በታማኝነት ሲያገለግሉ የነበሩት አቶ መንግስቱ ዘመነ ዘውዴ ባደረባቸው ህመም ምክንያት በህክምና ሲረዱ ቆይተው ኅዳር 4/ 2017 ዓ.ም ከዚህ አለም ድካም ማረፋቸውን ስንገልፅ በታላቅ ሀዘን ነው።
ለቤተሰቦቻቸው፣ ጓደኞቻቸው፣ የመቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን አባላት ፤ የስራ ባልደረቦቻቸው እና ለሚያውቋቸው በመሉ ታላቅ መጽናናትን እንመኛለን።
- የአስከሬን ሽኝት መርሃግብር በመቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን ዋና መስሪያ ቤት አርብ ኀዳር 6, 2017 ከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ ይከናወናል።
- የቀብር ስነስርዓቱ፣ አራት ኪሎ ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ግቢ ውስጥ በሚገኘው ቅዱስ በዓለ ወልድ ቤ/ክርስቲያን፣ አርብ ኀዳር 6, 2017ዓ.ም ከ ቀኑ 8፡30 ይፈጸማል።
በዚህ መራር የሃዘን ወቅትም ከቤተሰቦቻቸው ጎን በመሆን አጋርነታችንን እንድንገልጽ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።
ከልብ ከመነጨ ሀዘን ጋር
መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን እና ቤተሰቦቻቸው
About The Author


