MENA 31th General Assembly Meeting
የመቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን 𝟯𝟭ኛው ጠቅላላ ጉባኤ በስኬት ተጠናቀቀ!
[አዲስ አበባ – መጋቢት 19 ቀን 2018 ዓ.ም]
መቅድም ኢትዮጵያ ናሽናል አሶሴሽን (መኢና) ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ኃላፊዎች፣ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶችን ባለስልጣን ተወካዮች፣ የአህት ድርጅቶች መሪዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት 31ኛውን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤውን በድምቀት አካሂዷል፡፡
የጉባኤው ዋና ዋና ክንውኖች፦
*ተቋማዊ ግምገማ እና ዕቅድ፦ ጉባኤው የማህበሩን የ2025 በጀት ዓመት የሥራ እና የሂሳብ አፈጻጸም ሪፖርት በጥልቀት ገምግሞ አጽድቋል። በተያያዘም ለ2026 በጀት ዓመት የታቀዱ ስትራቴጂካዊ የሥራ እና የሂሳብ ዕቅዶች ላይ ተወያይቶ ውሳኔ አሳልፏል፡፡
- የመተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ፦ማህበሩ አሁን ካለበት ነባራዊ ሁኔታ ጋር እንዲጣጣም እና ቀጣይነቱን ለማረጋገጥ ታስቦ የተዘጋጀው፣ የአማካሪ ኮሚቴን በአዲስ መልክ ያካተተው ረቂቅ የመተዳደሪያ ደንብ በጉባኤው አማካኝነት ጸድቋል ።
*የቦርድ የአመራር ማጠናከሪያ፦ ጉባኤው የሁለት የሥራ አመራር ቦርድ አባላትን እጩነት መርምሮ፣ በተጓደሉ የቦርድ አመራሮች ቦታ ተተክተው እንዲሰሩ በሙሉ ድምፅ አጽድቋል።
በጉባኤው ማጠቃለያ ላይ ተሳታፊዎች በሙሉ በአዲስ መንፈስ እና በቁርጠኝነት የማህበሩን ተልዕኮ ለማሳካት፣ በተለይም የኤች.አይ.ቪ ኤድስ ስርጭትን ለመግታት እና በችግሩ የተጎዱ ወገኖችን ለመደገፍ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ዘርፈ ብዙ ሥራዎችን በጋራ ለመስራት ቃል ገብተዋል።
ይህ ጉባኤ ማህበራችን ባለፉት 31 ዓመታት ያስመዘገባቸውን ድሎች በማጠናከር ለቀጣይ የላቀ አገልግሎት ዝግጁ መሆኑን ያረጋገጠበት ታሪካዊ መድረክ ሆኖ ተጠናቅቋል፡፡
“ለተቋማዊ ቀጣይነትና ለላቀ ሰብዓዊ አገልግሎት በአንድነት እንቆማለን!”
Tags
About The Author


