በእምነት ተቋማት የሚከናወኑ የኤችአይቪ/ኤድስ ህክምና (𝗔𝗥𝗧) ክትትል እና ድጋፍ ስራዎችን ለመመልከት የመስክ ጉብኝት በሲዳማ ክልል ተደረገ
December 26, 2025 Comments Off on በእምነት ተቋማት የሚከናወኑ የኤችአይቪ/ኤድስ ህክምና (𝗔𝗥𝗧) ክትትል እና ድጋፍ ስራዎችን ለመመልከት የመስክ ጉብኝት በሲዳማ ክልል ተደረገ News Mena Admin

የመቅዲም ኢትዮጵያ (MENA) ዋና ስራ አስፈጻሚ፣ የፕሮግራም ቺፍ ኦፍ ፓርቲ (COP) እና የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ (IRCE) ከፍተኛ አመራሮች በሲዳማ ክልል፣ ሀዋሳ እና ይርጋለም ከተሞች በሚገኙ የሃይማኖት እና የመንፈሳዊ ህክምና ቦታዎች (Religious/Spiritual Healing Sites) ከፍተኛ የድጋፍ እና ክትትል ጉብኝት አድርገዋል።

#የጉብኝቱ ዓላማ፡-በእምነት ተቋማት የሚከናወኑ የኤችአይቪ/ኤድስ ህክምና (ART) ክትትል እና ድጋፍ ስራዎችን መገምገም እና ማጠናከር ነው።

#ዋና ዋና ነጥቦች፡-

#የህክምና እና እምነት ጥምረት፡ የፀረ-ኤችአይቪ ህክምናን (ART) ከመንፈሳዊ ህክምና (Spiritual Therapy) ጋር በማጣጣም፣ የእምነቱ ተከታዮች መድሃኒታቸውን ሳያቋርጡ መንፈሳዊ ተግባራቸውን እንዲያከናውኑ ግንዛቤ ተፈጥሯል።

#የሃይማኖት አባቶች ሚና፡ የሃይማኖት አባቶች ምእመናንን ወደ ኤችአይቪ ምርመራ በመምራት፣ ህክምና ያቋረጡትን በመመለስ እና አድልኦን እና መገለልን  በመቀነስ ረገድ እያበረከቱ ያለውን አስተዋጽኦ ለመመልከት ተችሏል።

ይህ ፕሮግራም እውን እንዲሆን ላደረገው የአሜሪካ መንግስት (USG) ላደረገው ድጋፍ ልባዊ ምስጋናችንን እናቀርባለን።

ለማህበረሰቡ ጤና የሚተጉ የሃይማኖት አባቶችን እናመሰግናለን                            

Tags
About The Author